Ayder Referral Hospital - Dean's Message

 

Dr. Abdulkadir Mehammed Seid Gidey


መቀሌ ዩነቪርሲቲ BPR’ን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል
 
BPR መሠረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ማለት ሲሆን የጤና ሣይንስ ኮሌጁም ይህንን መሠረታዊ የስረ ሒዴት ለውጥ በስራ ላይ እያዋለ እንደሆነ የኮሌጁን ዲን ዶ/ር አብዱልቃድር አስታወቁ።”...ሁል ጊዜ መያዝ ያለበት በአዲስ አስተሣሠብ ጥሩ ስራ ለመስራት መግባት ነው። የነበሩትን አስተሣሠቦች መተው መቻል አለብን። ስለዚህ በዋጋ፣በጥራትም በሠአትም በሁሉም ነገር ብቻ ውጤታማ የሆነ ስራ ለመስራት መቀየስ ማለት ነው። ስለዚህ ዋና መሠረት የሚያደርገው ደግሞ ተገልጋዩን ነው።” ሲሉ አብራርታዋል። 
 
 

…..BPR በመማር ማስተማር ሒደቱ ላይ ያመጣውንም ለውጥ ዶ/ር አብዱልቃድር እንደሚከተለው ያብራራሉ ”...ተማሪው መያዝ አለበት የምለው በፊት ካለንበት shift አድርገናል student center ትምህርት አሠጣጥን ነው የምንከተለው በህክምና ትንሽ ከበፊቱም ለየት ይላል በአብዛኛው case ተስጥቶ ስለሚሠራ student center component  ነበረው።…. አሁን ያለው አዝማሚያ በተማሪው አከባቢ የበፊቱን አስተሣሠብ አልለቀቀውም hand out   ይጠይቃል፣ አንዳንድ ነገሮች እንዲያልቁለት ይፈልጋል። መደረግ ያለበት ግን ትንሽ እንደመግቢያ ነገር ይሠጠዋል ከዛ በኋላ እሱ በተሠጠው አሣይመንት መሠረት እንዲያነብ ነው የሚፈለገው ይሄ የሚፈለግበት ምክንያት ምንድንድነው ራሱ ሀቁን ፈልጎ ማግኘት ስላለበት ነው ይሔ ለወደፊት በስፋት የምንሠራበት ስለሆነ ተማሪዎችም እየገባቸው ይሔዳል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ በስርአተ ትምህርቱ ላይ ያለው ትልቅ ለውጥ ይኔ ነው።” ከዚህ በተጨማሪም መምህራን በየጊዜው ፈተና እና assignment     እያዘጋጁ የተማሪውን ለውጥ የሚያይበት ሁኔታ ስላለ ለተማሪውም ለአስተማሪውም ጥሩ የሆነ environment  ይፍጥራል ብለዋል- ዶ/ር አብዱቃድር።

 

የትምህርት አሠጣጡ ተማሪ ተኮር ከመሆኑም በተጨማሪ remedial program ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለፀ። የፈተና አሠጣጡም መጀመሪያ በ50% progress assessment የሚያለቅ ሲሆን final exam ደግሞ 50% ይይዛል። ስለዚህ ከመጀመሪያው 50% ላይ ድክመት ያለበት ተማሪ final ከመፈተኑ በፊት ወደ ተማሪዎች አገልግሎት ተልኮ እስፈላጊውን ድጋፍ ይደረግለታል። ይህም እንደ ትልቅ ለውጥ እንደሚታይ አስረደተዋል-ዶ/ር አብዱልቃድር:: በማያያዝም “ በማባረር ጥራት ይጠበቃል የሚል እምነት የለንም። በማስተማር ግን ጥራትን ማስጠበቅ ይቻላል።” ብለዋል

በሌላ በኩል የኮሌጁ ሠራተኞች BPR’ን ምን ያህል ተቀብለውታል ለተግባራዊነቱስ ምን ያህል አየሠሩ ነው ተብሎ ለተነሣላቸው ጥያቄ የሚከተሉውን ምላሸ ሠተዋል - ዶ/ር አብዱልቃድር

አብዛኛው ሠራተኛ ተቀብሎታል የጎላ ተቃውሞም የለም። ሁል ጊዜ ወደ አዲስ ነገር ስትገባ ግልፅ ያለሆኑ ነገሮች ይኖራሉ እነሱን በሒደት ስራ ላይ ገብተህ ስትፈትሻቸው እየጠሩ የሚሄዱበት ሁኔታ አለ በዚህ ደረጃ በመጀመሪያ አከባቢ አንዳንድ ግራ መጋባት አይነት ነገሮች ከመኖረቸው ውጪ የጎላ ተቃውሞ አልነበረም በተከታታይ ባደረግናቸው ውይይቶች አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ደርሷል።” ብለዋል አያይዘውም “ ….መቶ በመቶ ማንንም ማስደሠት አይቻልም። የታመነበትና አብዛኛውን ሠው 

የሚያግባባ ነገር እየተሠራ የሚሔድበት ስርአት ነው -የኔ ትክክል ነው ያንተ ስህተት ነው እያልክ የምትሟገትበት አይደለም ሁሉም የተለያየ አመለካከት የተለያየ መንገድ አለው። እኔ የመረጥኩት መንገድ ከሌላው የተሻለ ሊሆን ይችላል ወይ ደግሞ ያኛው የተሻለ ሊሆን ይችላል በሂደት ግን እየተፈተሸ የተሻለ የተሻለውን እያስገባን የምንሔድበት ነው ያለው። ስለዚህ ሀሉም idea ተቀባይነት ይኖረዋል። ነገር ግን መግባባት ላይ ደርሠን standard ብለን ያስቀመጥነው ነገር ሌላ በጣም አሣማኝ የሆነ ሆኖ ሀሣብ የሚያስቀይር የተሻለ ነገር እስኪመጣ ድረስ ግን በዛ     መገዛት ግድ ነው። አለበለዛ ስርአት አልበኝነት ይነግሣል ማለት ነው እኛ የምናደረገው ነገር ስርአቱን እንዲከበር ካልሆነ በስተቀር የማንንም አመለካከት ለመድፈቅ የሚሠራ ነገር አይኖርም ።” ብለዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር አብዱልቃድር ለግቢው ማህበረሠብ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።
          “አንድ ተረት ልናገር ምናልባት ከዚህ በፊት አቅርቤው ከሆነ አላውቅም አንዲት እናት ሦስት ልጆች ነበሯት አሉ ለኩራዝ የሚሆን ነዳጅ አስፈለጋትና ትንሹን ልጅ ትልከዋለች-አስር ብር ሠጥታው ልጁ ገዝቶ ሲመለስ መንገድ ላይ ይወድቃል ሲነሣ ግማሹ ነዳጅ ተደፍቷል። ከዚያ እያለቀሠ ቤት ይገባል። ልክ ቤት ሲገባ ታላቅ የነበረው ይስቃል ። ምንድነው ሲባል ግማሹ ፈሠሠብኝ ብሎ ለናቱ ይሠጣታል። እናት በቃ ምንም አይደለም ብላ ትልቁን ልጅ ትጠራና 10 ብር ሠታ እሱ እንዲገዛ ትልከዋለች። እሱም ይሔድና ገዝቶ ሲመለስ ይወድቃል ሲነሣ ልክ እንደበፊተኛው ልጅ ግማሽ ነው የቀረው። ይህንን ሲያል ብራቮ “ግማሹን አዳንኩት” ይላል። ከዛ ለናቱ ይሰጣታል ይህን ያየች እናት የማህከለኛውን ልጅ ትጠራና እሱንም 10 ብር አሲዛ እንዲገዛላት ላከችው ይህም ልጅ ገዝቶ ሲመለስ ይወድቃል። ሲነሣ እሱም እንደ ወንድሞቹ በእጁ ላይ የቀረው ግማሹ ብቻ ነው። ግማሹን ያይና ቆም ብሎ ሲመለከት አከባቢው ላይ እቃ የሚጭኑ ሠዎች ያያል ከዚያ በኋላ ይሔድና እቃ ጫን ጫን አድርጎ 5 ብር ይሠጡታል በ5 ብር የጎደለውን ነዳጅ ይሞላና ወደ ቤቱ ይዞ ይሔዳል። ከዛ ለናቱ ሙሉ ያሰረክባል። ከዛ ምን ሆነህ ቆየህ ሲሉት “ሦስታችንም ያጋጠመን አንድ አይነት ሁኔታ ነው ልዩነቱ እኔ ሙሉ ይዠ መጣሁ አላቸው::
የዚህ መልዕክት ምንድነው? የመጀመሪያው ልጅ ያለቀሠው negative attitude ስላለው ነው ሁለተኛው ልጅ ደግሞ positive attitude ስላለው ነው::: ያለውን በAction”አልተደገፈም ሦስተኛው ግን positive attitude አለው የጎደለችውንም ምልቶ ነው የመጣው።
ስለዚህ ይህ መልክት ለሁሉም ነው ለተማሪውም ለግቢውም ሁልጊዜ ምንድነው ይሔ ጎደለ ይሄ ጎደለ ነው የሚባለው ግን አጠገባችን የጎደለ ነገር መሙያ ዞር ዞር ብለን ብናይ ሞልቷል ለማለት ፈልጌ ነው positive attitude n Action ካልተደገፈ በቂ አይደለም ብዙ    ሰዎች positive attitude እንዳላቸው አውቃለሁ እነዛን ደግሞ ትንሽ በተግባር ገፉ ቢያደርጉ ብዙ ለውጥ ይመጣል የሚል እምነት አለኝ አመሰግናለሁ ።” 
 
 
 
Today, there have been 13 visitors (17 hits) on this page!
This website was created for free with Own-Free-Website.com. Would you also like to have your own website?
Sign up for free